ቻይና በ2018 ለጠፈር ምርምር የሚውሉ 35 ሮኬቶችን ወደ ህዋ ለማስወንጨፍ አቅዳለች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይና በአውሮፓውያኑ 2018 በያዘችው የጠፈር ምርምር መርሀ ግብር መሰረት ቢያንስ 35 ሮኬቶች ለማስወንጨፍ ማቀዷ ተመለከተ።

የሀገሪቱ ኤሮስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን እንዳስታወቀው፥ ከሚወነጨፉት ሮኬቶች መካከል ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ የገነባቻቸው ይገኛሉ ተብሏል።

ኮርፖሬሽኑ እንደገለፀው፥ ለማስወንጨፍ የታቀዱት የሮኬቶች ቁጥር በታሪኩ ከፍተኛው ነው።

ከሚያስወነጭፉቸው ሮኬቶች ብዛት እና ግዙፍ ፕሮጀክቶቹ ከሚደርሱበት ወሳኝ ምእራፍ አንፃር 2018 ፈታኝ ዓመት እንዲሚሆንበት ነው ኮርፖሬሽኑ ያስታወቀው።

ሆኖም ተልእኮዬን ለማሳካት ወደኋላ አልመለስም ብሏል።

ኮርፖሬሽኑ የተለያዩ ግቦችን ያስቀመጠበትን 2025 የሚል ማኑፌስቶ በቅርቡ ይፋ አድርጓል።

 

ምንጭ፦ ሲ.ጂ.ቲ.ኤን.