አፕል ወደፊት የሚያመርታቸው ስልኮች ያለገመድ ባትሪያቸው የሚሞላ ይሆናል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2010 (ኤፍ. ቢ. ሲ.) አፕል ኩባንያ፥ ባትሪን ያለ ገመድ ሀይል መሙላት የሚችሉ አይፎን ስልኮችን ማምረት እንደሚጀመር ገለፀ።

ኩባንያው ለአሜሪካ የፈጠራ እና የንግድ ምልክት ተቋም ባስገባው የፈጠራ ባለቤትነት መጠየቂያ ሰነድ ላይ ያለ ገመድ ሀይል ለሚሞሉ የአይፎን ስልኮች እውቅና የሚጠይቅ ነው።

በዚህ እውቅና ባገኘው ቴክኖሎጂ መሰረት አፕል ወደፊት የሚያመርታቸው ስልኮች ያለገመድ ከቻርጀሮቻቸው ጋር ተገናኝተው ሀይል መሙላት የሚችሉ ናቸው።

ገመድ አልባው የሀይል መሙያ ቻርጀሩም በአንድ ጊዜ ከአንድ የሚበልጡ ስልኮችን ሀይል መሙላት እንደሚችል ነው የተገለፀው።

ለባለቤትነት ፈቃድ የቀረበው ሰነድ እንደሚያስረዳው ይህ ያለገመድ ሀይል የሚሞላው ቴክኖሎጂ ከስልክ ውጪ ለላፕቶፕ፣ ዴስክቶፕ ኮምፒውተር እና ታበሌቶችም እንደሚሆን ይጠቁማል።

በዚህ ቴክኖሎጂ መሰረት ሀይል የሚሞላውም ሆነ የሚሞላው በገመድም ያለገመድም መገናኘት ይችላሉ። 

ምንጭ፦www.techworm.net