ባይተን ኩባንያ አዲስ የስማርት መኪና ሞዴልን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) ባይተን ኩባንያ አዲስ የስማርት መኪናን ለእይታ አቀረበ።

ለእይታ የቀረበው ዘመናዊ ተሽከርካሪ፥ የመኪና አምራች ቢ ኤም ደብሊው እና የስማርት ኤሌክትሮኒክስ አምራች ኩባንያው አፕል የቀድሞ ሰራተኞች በጋራ ያመረቱት ነው ተብሏል።

የመኪናው አምራች ኩባንያ ሰዎች ወደፊት ከፈረስ ጉልበት ይልቅ ለዲጂታል ጉልበት እንደሚጨነቁ በማንሳት ተሽከርካሪው ምን ያህል የመጪው ጊዜ ቴክኖሎጂን የያዘ መሆኑን አንስቷል።

ሆኖም ባለሙያዎች በተሽከርካሪው ጋቢና ውስጥ ያለው ሰፊ ስክሪን ከሀይል መሙያ ጋር ተያይዞ እጥረቶች እንዳሉበት ነው እያነሱ ያሉት።

በመኪናው ጋቢና ውስጥ ያለው ሰፊ ስክሪን ሰዎች ከመኪና ውጪ ያሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎቶችን መኪናው ውስጥ ሆነው እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን ኩባንያው ተናግሯል።

ስክሪኑ የቀንም ሆነ የምሽት ሁኔታን ባገናዘበ እና በማይረብሽ ሁኔታ የሚሰራ ሲሆን፥ በድምፅ እና በንኪኪ እንደሚታዘዝ ነው የተመለከተው።

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ