የእጅ ጣታችንን እንደ ስልክ የሚያስጠቅመው ቴክኖለጂ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኤስ.ጂ.ኤን.ኤል የተባለው እንደ ሰዓት በእጃችን ላይ የሚታሰር ቴክኖሎጂ የእጅ ጣታችንን እንደ ስልክ ያስጠቅመናል ተብሏል።

ቴክኖሎጂው በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር የፊታችን መጋቢት ወር 2018 ይለቀቃል የተባለ ሲሆን፥ እንደ ሰዓት በእጅ የሚታሰሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይም አዲስ እብዮት ይዞ እንደሚመጣ ነው የተነገረው።

ምርቱ የሳምሰንግ ሲ ላብ ነው መሆኑ የተነገረለት ይህ ቴክኖሎጂ፥ በአሜሪካ ላስ ቬጋስ በተካሄደ የቴክኖሎጂ አውደ ርእይ ላይ ነው ለእይታ የቀረበው።

በአውደ ርእዩ ላይ ቀርበውን ቴክኖሎጂ የሞከሩ ሰዎችም፤ በእጅ ላይ የሚታሰረውን ሰዓት መሳይ ነገር በማሰር ጆሯቸው ላይ ጣታቸውን አስቀምጠው ሙዚቃ ማዳመጥ መቻላቸውን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ቴክኖሎጂው ሰዎች በእጅ ጣታቸው ብቻ ተጠቅመው ስልክ ለመደወል እና የተደወለላቸውን ጥሪ ተቀብለው ማነጋገር ያስችላቸዋል ተብሏል።

በእጅ ላይ የሚታሰረው ቴክኖሎጂው የአንድሮይር ኦፕሬቲንግ ሲስተም እና የአይፎን አይ ኦ ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን መጠቀም እንዲችል ተደርጎ ነው እየተሰራ ያለው።

ምንጭ፦ www.techworm.net