5 ከጎግል ላይ መረጃ ማፈላለጊያ ዘዴዎች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አንድ ሰው ከኢንተርኔት ላይ መረጃ ለማውጣት ኮምፒውተሩን ከከፈተ በኋላ አብዛኛውን ጊዜ የሚጎበኘው ጎግል የተሰኘውን የመረጃ መፈለጊያ ድረ ገጽ ነው።

እዚህ ድረ ገጽ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የመረጃ ሰብስቦች ተቀምጠው ይገኛሉ ሆኖም ግን እነኚህን መረጃዎች ፈልገን የምናገኝበት መንገድ የምናገኘውን መረጃ ውስንነት እና ጥራት ይወስነዋል።

እኛም ከጎግል ላይ መረጃ ስንፈልግ የምንፈልገውን መረጃ በብዛት እና በጥራት ሊያስገኙልን የሚችሉ የአፈላለግ መንገዶችን እንጠቁማችሁ፦

1 የምንፈልገውን መረጃ በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ በማድረግ መፈለግ (“”)

ይሄ በብዛት የሚታወቅ መፈለጊያ ዘዴ ሲሆን፥ እናንተ የምትፈልጉትን ቃላት ወይንም መረጃ የያዙ ገጾችን ብቻ መርጦ እንዲያመጣም ያደርጋል።

2 የኮከብ (*) ምልክትን በመጠቀም የማይታወቁ ቃላት ወይንም ሀረግን መፈለግ

የማይታወቅ ወይም እንግዳ የሆነ ቃል ወይም ሀረግን የኮከብ ምልክትን ከቃሉ ወይም ሀረጉ አስቀድምን በመጠቀም መፈለግ የተሻለ ውጤት ለማግኘት እንደሚረዳ ይንገራል።

ለምሳሌ፡ (e.g. “* is thicker than water”). ወይንም ደግሞ እንግዳ የሆነው ቃል በአርፍተ ነገሩ መሀል ላይ የሚገኝ ከሆነ (e.g. “imagine all the * living for today”) በማድረግ መፈለግ ይቻላል፡፡

3 የሰረዝ የመቀነስ ምልክትን መጠቀም(-)

የእናንተ ፍላጎት ያልሆኑ ግን ለመፈለግ ከፃፉት ሀረግ ውስጥ ያሉ ፊደሎችን ውጤት እንዳያመጣ ከሀረጉ መሀል የመቀነስ ምልክትን መጠቀም።

አንድ መጠሪያ የሆነ ነገር ወይም ረዘም ያለ ሀረግ ለመፈለጊያነት ጎግል ላይ በምትጽፉበት ወቅት አንዱን ቃል በመምረጥ የእሱን ውጤት ብቻ እንዳያመጣ በምትፈልጉት ቃላት መሀል የመቀነስ ምልክትን በመጠቀም ይህን ማስቀረት ትችላላችሁ፡፡

ለምሳሌ፡ ( jaguar -car)

4 የሁለት ነገሮችን ልዩነት ወይም አንድነት ለማወቅ ከፈገለጋችሁ “vs.” በመጠቀም መፈለግ

ለምሳሌ እራትዎን በርገር ወይም ፒዛ ለመብላት ፈልገው ሁለቱን ማወዳደር ቢፈልጉ ሁለቱን በ “vs.” ጎን ለጎን አድርጎ በመጻፍ የሁለቱንም መረጃ ጎን ለጎን ሆኖ ማግኘት ትችላላችሁ

5 ምስሎችን ምስልን በመጠቀም መፈለግ

የሚያቁት የመሰሎትን ፎቶ አስተውለው ከየት እንደመጣ እና ሌላ ተመሳሳይ ፎቶ እንዳለው ማወቅ ከፈለጉ ጎግል ላይ በመሄድ የካሜራ ማንሻ ቁልፍ የምትመስለዋን በመጫን ፎቶውን ከኮምፒውተርዎ ወደ ጎግል በማስገባት ተመሳሳዩን ፎቶ እና መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ምንጭ፦ ታይም መጽሄት