ኢንስታግራም “ታይፕ ሞድ” የተባለ አዲስ አገልግሎት አስተዋወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ የሆነው ኢንስታግራም “ታይፕ ሞድ” የተባለ አዲስ አገልግሎት ማቅረቡ ተነግሯል።

“ታይፕ ሞድ” የተባለው አዲሱ የኢንስታግራም ማሻሻያ ተጠቃሚዎች በገጹ ላይ ከፎቶ ግራፋቸው ጋር አሊያም ያለ ፎቶግራፍ የተለያዩ ጽሁፎችን ለመጻፍ እና ለማጋራት የሚያስችል ነው።

በዛሬው እለት ይፋ የተደረገው አገልግሎቱ በተለያዩ ፎንቶች ለመጻፍ የሚያስችል ሲሆን፥ ጽሁፉንም በተለያዩ ቀለማት በማሸብረቅ ለማቅረብ ያስችለናል።

instagram_t2.jpg

“ታይፕ ሞድ” የተባለውን አገልግሎት ማንኛውም የኢንስታግራም ተጠቃሚ በአይ.ኦ.ኤስ እና አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ስማርት ስልኩ ላይ መጠቀም ይችላል ነው የተባለው።

አገልግሎቱን ለመጠቀምም መጀመሪያ የኢንስታግራም መተግበሪያችነን ከከፈትን በኋላ፤ ከስልካችን በስተግራ በኩል ያለውን የካሜራ ምልክት በመንካት መክፈት አለብን።

ከከፈትን በኋላም ከስልካችን ግርጌ ላይ የተለያዩ አማራጮች የሚመጡልን ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ “TYPE” የሚለውን በመምረጥ የፈለግነውን ፅሁፍ በመጻፍ ማጋራት እንችላለን።

የፌስቡክ ኩባንያ ንብረት የሆነው ኢንስታግራም እስካሁን የተለያዩ ፎቶ ግራፎች እና ቪዲዮዎችን የማጋራት አገልግሎት ብቻ ነበር ሲሰጥ የነበረው።

ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk