ፌስቡክ የፈቀዳቸውና የከለከላቸው ተግባራት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ፌስቡክ በማህበራዊ ድረ ገጹ ላይ ልናከናውናቸውና ከማድረግ ልንቆጠብ በምንችላቸው ነጥቦች ዙሪያ አዲስ ህግ አውጥቷል።

አንዳንድ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ድረ ገጹን ላልተገባ ተግባር እየተጠቀሙበት መሆኑን ተከትሎ ነው ፌስቡክ ህጎቹን ለማውጣት የተገደደው።

አዲሱ ህግ በአለማችን በርካቶችን እያስተሳሰረ በሚገኘው ፌስቡክ ላይ ምን መጫን እንደሚቻልና እንደማይቻል በግልጽ ተቀምጧል።

1. እርቃን

ያልተፈቀደ

ማንኛውም የግብረ ስጋ ግንኙነትን የሚያሳዩ እርቃን ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች፣ የተለያዩ ስሜት ቀስቃሽ የሰውነት ክፍሎችን የሚያሳዩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ፌስቡክ ላይ መለጠፍ አይቻልም ይላል የመጀመሪያው ህግ።

የተፈቀደ

ጡት ማጥባትን የሚሰብኩ እናቶች፣ የጡት ቀዶ ጥገናን የሚገልጹና ህያው ያልሆኑ እርቃን ቅርጻቅርጾችና ሀውልቶችን የሚያሳዩ ፎቶ ግራፎችን መለጠፍ ይቻላል።

2. የጥላቻ ንግግሮች

ያልተፈቀደ

ጾታ፣ ዘር፣ ሀይማኖት፣ ብሄር፣ የወሲብ አመለካከትና አካል ጉዳተኝነትን መሰረት በማድረግ ሰዎችን በቀጥታ መዘለፍ የተከለከለ ነው።

የተፈቀደ

የህብረተሰቡን ንቃተ ህሊና የሚያሳድጉና ስለ ጥላቻ ንግግሮች የሚያስተምሩ ነጥቦችን ማጋራት የተፈቀደ ነው።

ቀልዶች፣ በተለያዩ ጉዳዮች የሚናፈሱ አሉባልታዎችን መተቸትና የማህበረሰቡን አመለካከት በተረጋገጠ እና እውነተኛ በሆነ የፌስቡክ አድራሻችን ላይ መለጠፍም በፌስቡክ ተፈቅዷል።

3. ግጭት ቀስቃሽ ምስሎች

ያልተፈቀደ

አሰቃቂ ምስሎችና ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን ማጋራት
የተፈቀደ

የሚጋሩት ምስሎች ግጭትን ከማባባስ ይልቅ ግንዛቤን ለማሳደግና የሰብአዊ መብት ረገጣን የሚያሳዩ፣ የሽብር ድርጊቶችን ወይም ሌላ የህዝብ ጉዳይን የሚያሳዩ ከሆነ ግን ፌስቡካችን ላይ መለጠፍ ትችላላችሁ ተብሏል።

4. ራስን መጉዳትን የሚያሳዩ ነገሮች

ያልተፈቀደ

ራስን ማጣፋትን ወይም መጉዳትን የሚያበረታቱና የሚያሳዩ ምስሎችና መረጃዎች

የተፈቀደ

ራስን መጉዳት ወይም ማጥፋት የሚያደርሰውን ጉዳት የሚያስረዱ ምስሎች ወይም መረጃዎችን መለጠፍ፤

የሰውነት ክብደት ወይም ቅርጽ ለውጥን የሚያሳዩ ምስሎች በፌስቡክ ራስን ወይም ሰውነትን እንደመጉዳት አይወሰድም።

ፌስቡክ በተጨማሪም የተለያዩ ዛቻ እና ማስፈራሪያዎችን መልዕክቱን ወይም ምስሎቹን በሚያጋሩት ሰዎች ታአማኝነት እና በሚኖሩበት ሀገር በመመሰረት የማጣራት ሰር እንደሚሰራም አስታውቋል።

ምንጭ፦ news.sky.com