ሄሊኮፕተር እና ሎደር የሰራው የጋምቤላው ወጣት

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አዲስ አበባ በተዘጋጀው ውድድር ላይ ጎር አኬሎ ትንንሽ ሄሊኮፕተር እና ሎደር በመስራት ለመጨረሻው ፉክክር ቀርቧል፡፡

የጎር ሁለቱም ስራዎች መሬት ወርደው እውን መሆን በሚያስችላቸው ሁኔታ የተሰሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ጎር አኬሎ የ19 ዓመት ወጣት ሲሆን ጋምቤላ በሚገኘው ኦፔኖ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት በመማር ላይ ይገኛል፡፡

ጎር ከዚህ በኃላ ከስምንት የተለያዩ ክልል ከተሞች ከመጡ አሸናፊዎች ጋር ለመወዳደር ተዘጋጅቷል፡፡

ጎር አዲስ አበባ የሚመጣው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው ሶልቭ ኢት በተሰኘ ውድድር ላይ አሸንፎ ነው ተብሏል፡፡

ለሁለቱ ስራዎቹ የተጠቀመባቸው ቁሳቁሶች ካገለገሉ የኤሌክተትሮኒክስ ውጤቶች ሲሆኑ ሞተሮቻቸውንም እንዲሁ ካገለገሉ ስልኮች ላይ መጠቀሙን ተናግሮዋል፡፡

ወደፊት ትልቅ ፋብሪካ የመክፈት ፍላጎት እንዳለው የተናገረው ጎር አሁን ላይ በልጆች የአሻንጉሊት ምርቶች ላይ መሳተፍ እንደሚፈልግ ተናግሮዋል፡፡