ግብጻውያን ወጣቶች ፍጆታው አየር ብቻ የሆነ ተሸከርካሪ ሰሩ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ግብጻውያን ወጣቶች አንድ ሰው የመያዝ አቅም ያለው ፍጆታው አየር ብቻ የሆነ ተሸከርከሪ መስራታቸውን አስታወቁ፡፡

የተማሪዎቹ ፈጠራ አካባቢን ከብክለት የሚታደግ እንዲሁም ነዳጅ የማይፈልግ በመሆኑ ትልቅ እምርታ ነው ተብሎለታል፡፡

ወጣቶቹ ተሸከርካሪውን የሰሩት ለመመረቂያ ፕሮጀክታቸው ሲሆን በሀገራቸው እየናረ የመጣውን የኃይል አቅርቦት መፍትሔ ለመስጠት በማሰብ ነው ብለዋል፡፡

ይህ ባለአንድ ሰው ተሸከርካሪ መኪና በሰዓት 40 ኪሎሜትር የመጓዝ አቅም እንዳለው ገልጸው ወደፊት በሰዓት 100 ኪሎሜትር እንዲሸፍን ማሻሻያዎችን እየሰሩ እንደሚገኙም ጠቅሰዋል፡፡

እንዲሁም በየ30 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ ኦክስጂን እንደምትሞላም ወጣቶቹ ተናግረዋል፡፡

ተሽከርካሪው ለመገንባት 18 ሺ የግብጽ ፓውንድ ወይንም አንድ ሺህ ዶላር ወጪ እንደጠየቀም ተማሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

 

4EEF746800000578-0-image-a-10_1533799624853.jpg4EEF8D1D00000578-0-image-a-13_1533799639842.jpg

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 


ምንጭ፦ሜይልኦንላይን
በአብርሃም ፈቀደ