አዲሱ ሳምስንግ ጋላክሲ ኖት 9 የምንነሳው ፎቶ የማያምር ከሆነ ቀድሞ የሚጠቁም ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሁኑ ወቅት የስማርት ስልክ አምራቾች ምርታቸው ተወዳዳሪ እንዲሆን የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በሚያመርቱት ስልኮች ላይ እያካተቱ ነው።

ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የሆነው ሳምሰንግም ከሰሞኑ ጋላክሲ ኖት 9 ስማርት ስልኩን ያስተዋወቀ ሲሆን፥ አዳዲስ ፈጠራዎች እንደተካተቱበትም ለማወቅ ችለናል።

ከእነዚህም ውስጥ የበርካቶችን ቀልብ የሳበው የካሜራው ጉዳይ ነው የተባለ ሲሆን፥ ካሜራው የምንነሳው ፎቶ ግራፍ የማያምር አሊያም ችግር ያለበት ከሆነ ቀድሞ የሚጠቁም መሆኑ ነው።

የሳምሰንግ ጋላክሲ ኖት 9 ካሜራ በተገጠመለት ሶፍትዌር አማካኝነትም የምንነሳው ፎቶ ግራፍ ብዥታ ካለበት አሊያም በብዛት የምንነሳ ከሆነ አንዳችን ከመሃል ከጨፈንን የመለየት አቅም አለው ተብሏል። 

Note_9_2.jpg

ሳምሰንግ አሁን በስልኩ ላይ ይዞት የመጣው ፈጠራም በተለይም እንደ ሁዋዌይ ካሉ የስማርት ስልክ አምራቾች የሚገጥመወን ፉክክር ለማሸነፍ ይረዳዋል ተብሏል።

ከካሜራው በተጨማሪም አዲሱ የሳምሰንግ ጋላክሲ ኖት 9 በርከት ያሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የተገጠሙለት መሆኑም ተነግሯል።

ከእነዚህም ውስጥ ያለምንም ገመድ ከርቀት ስልኩን ለማዘዝ የሚያስችል ከርቀት መቆጣጠሪያ (ሪሞት ኮንትሮል) ጋር የሚመሳሰል ቀጠን ያለ መሳሪያም ተሰርቶለታል።

Note_9_3.jpg

እንዲሁም ባትሪውም ከዚህ ቀደም ከተሰሩ የሳምሰንግ ስማርት ስልኮች የተሻለ መሆኑ ተነግሯል።

ስማርት ስልኩ ከ10 ቀናት በኋላ ለገበያ ይቀርባል ተብሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ