በጋዛ ከሆዳቸው በታች ተጣብቀው የተወለዱት ህፃናት በተሳካ ቀዶ ጥገና ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) የሳዑዲ ሃኪሞች በጋዛ በሆዳቸው እና ከዚያ በታች ባለው የአካል ክፍላቸው ተጣብቀው የተወለዱ ህፃናትን በተሳካ ቀዶ ጥገና አለያይተዋቸዋል።

ፋራህ እና ሃኔን የተባሉት ሁለት ሴት ህፃናት፥ የቀዶ ህክምና የተደረገላቸው በሪያድ ውስጥ በሚገኘው የንጉስ አብደላህ የህፃናት ሆስፒታል ነው ተብሏል።

ህፃናቱ የየራሳቸውን ልብ እና ሳምባ ይዘው ቢወለዱም ከሆዳቸው ጀምሮ የጋራ እግር ይዘው ነው የተወለዱት።

_98446648_f9b2da37-8191-4dbd-b7bf-65ec4f44f839.jpg

የህፃናቱ ህይወት አደጋ ላይ እንደሚወድቅ የጋዛ ዶክተሮች ከተናገሩ በኋላ፥ ልጆቹ ከአባታቸው ጋር ወደ ሳዑዲ አረቢያ እንዲጓዙ መደረጉም ተገልጿል።

ሀኪሞቹን ዋቢ በማድረግ የሳዑዲ አረቢያ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፥ ቀዶ ህክምናው በተሳካ ሁኔታ ተፈፅሟል።

ቀዶ ጥገናው የአንጀት፣ የጉበትን እና የሆድ ዕቃን ለመለየት ዘጠኝ ደረጃዎችን ያካተተ ነበር።

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ