ተማሪዎች ቆመው እንዲማሩ ማድረግ በልጅነት የሚከሰት ከልክ ያለፈ ውፍረትን መከላከል ይቻላል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህፃናት በትምህርት ቤት ውስጥ በመማር ላይ እያሉ በመሃል እንዲቆሙ ማድረግ በልጅነት የሚከሰት ከልክ ያለፈ ውፍረትን ለመከላከል ይረዳል ተባለ።

በህፃናት ዙሪያ የተለያዩ ጥናቶችን ያካሄዱት ዶክተር ራንጋን ቻተርጄ፥ ተማሪዎች ሁሌም ወንበር ላይ ተቀምጦ እንዲማሩ ከማድረግ ይልቅ በመካከል ለየተወሱ ሰዓታት እንዲቆሙ ማድረግ መልካም ነው ይላሉ።

በዚህ ዙሪያ በተሰራ ጥናትም ተማሪዎች የቁም ጠረጴዛን ተጠቅመው እንዲማሩ በማድረግ ጠቀሜታውን ለማወቅ ተችሏል።

በዚህም ተማሮዎች በቀን ለ3 ሰዓት የቁም ጠረጴዛን ተጠቅመው ቆመው እንዲማሩ የተደረገ ሲሆን፥ ለተከታታይ 5 ቀናት የቁም ጠረጴዛን እንዲጠቀሙ ተደርጓል።

በዚህም ህፃናት ተማሪዎቹ በ5 ቀናት ቆሞ የመማሪያ ጊዜያቸው ከ30 ሺህ በላይ አላስፈላጊ ካሎሪን ማቃጠል እንደቻሉ በጥናቱ ተለይቷል ነው የተባለው።

ይህ የካሎሪ መጠንም አንድ ሰው 10 የማራቶን ሩጫዎችን ሩጦ ከሚያቃጥለው የካሎሪ መጠን ካር ተመጣጣኝ መሆኑንም በጥናቱ ተመልክቷል።

ስለዚህ ይላሉ ዶክተር ራንጋን ቻተርጄ፥ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎቻቸው ተቀምጠው የሚማሩበትን ወንበር እና ጠረጴዛ በሚያሰሩት መጠን የቁም የመማሪያ ጠረጴዛዎችንም ቢያሰሩ መልካም ነው ብለዋል።

የሁለት ልጆች አባት የሆኑት ዶክተር ራንጋን ቻተርጄ፥ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ልክ እንደ መቀመጫ ሁሉ የቁም ጠረጴዛዎችን ማየት እሻለሁ፤ ልጆችም ከመቀመጥ ይልቅ መቆምን አብዝተው እንፈዲመርጡ አመክራለሁ ሲሉም ተናግረዋል።

ለህፃናት በቀን ውስጥ ለ6 ሰዓታት ተቀምጦ በትምህርት ማሳለፍ ለጀርባ ህመም እና ከመጠል ላለፈ የሰውነት ውፍረት እና ክብደት እንዲጋለጡ ያደርጋል ይላሉ ዶክተር ራንጋን ቻተርጄ።

ከዚህ በተጨማሪም በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚሸጡ ጣፋጭነት የበዛባቸው ምግቦች እና መጠጦች ህጻናትን ከመጠን ላለፈ ውፍረት እየዳረገ ነው ብለዋል።

ስለዚህም በትምህርት ቤቶች አካባቢ እድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት ጣፋጭነት የበዛባቸው ምግቦች እና መጠጦች መሸጥ የለባቸውም ባይ ናቸው ዶክተር ራንጋን ቻተርጄ።

 

ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk