በሳምንት አንድ ጊዜ የሚወሰድ የኤች አይ ቪ መድሃኒት በእንስሳት ላይ ተሞክሮ ተስፋ ሰጥቷል

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካውያን ተመራማሪዎች በሳምንት አንድ ጊዜ የሚወሰድ የኤች አይ ቪ መድሃኒት በአሳማዎች ላይ ተሞክሮ ውጤት ማሳየቱን ተከትሎ በሰው ላይ ሊሞክሩ መሆኑ ተነገረ።

ተመራማሪዎቹ ይህ መድሃኒት ታካሚዎች በየቀኑ መድሃኒት ከመውሰድ የሚታደጋቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ 4 ሴንቲሜትር የኮከብ ቅርጽ ያለው አዲስ በተመራማሪዎች የበለፀገውን የኤች አይ ቪ መድሃኒት፣ በሆድ ውስጥ ለሰባት ቀናት በመቆየት የመድሃኒት መጠኑን በየጊዜው ለታካሚው ይለቃል ነው የተባለው።

መድሃኒቱ ዝንጀሮን ጨምሮ በሌሎች አጥቢ እንስሳት ቢሞከር የሚል ሀሳብ ቢሰጥም ተመራማሪዎች በሁለት ዓመት ውስጥ በሰው ላይ መሞከሩ ይሻላል የሚል አቋም አላቸው።

ባለሙያዎች እንደሚሉት አዲሱ የሕክምና አማራጭ ጥሩ ቢሆንም፥ በሳምንት አንድ ጊዜ ሰዎች የሚውጡት ይህ የኤች አይ ቪ መድሃኒት አሁንም ሊሻሻል ይገባል።

አዲሱ መድሃኒት ረዥም ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሆድ ውስጥ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ ቢሆንም ነገር ግን በትንሹ አንጀት በመግባት የምግብ መፈጨት ስርአትን እንደማያዛባ ተነግሯል።

 

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ