በጣም የሚያቃጥል ሻይ የጉሮሮ ካንሰር ተጋላጭ ያደርጋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አልኮል ከመጠን በላይ የሚጠጡ አሊያም ሲጋራ የሚጨሱ ሰዎች በጣም ትኩስ የሆነ ሻይ አዘውትረው የሚጠጡ ሰዎች ለጉሮሮ ካንሰር ተጋላጭነታቸውን እንደሚጨር በቻይና የተሰራ ጥናት አመልክቷል።

በቀን ውስጥ በጣም የሚያቃጥል ሻይ እና አልኮል የሚጠጡ ሰዎች ለጉሮሮ ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው በ5 እጥፍ የጨመረ መሆኑን ጥናቱ ያመለከተ ሲሆን፥ ይህ አሃዝ ሲጋራ ለሚያጨሱትም ተመሳሳይ ነው ተብሏል።

የጥናቱ አልኮል እና ሲጋራ አብዝተው የሚያዘወትሩ ሰዎች ትኩስ ሻይ ከመጠጣት ቢቆጠቡ መልካም መሆኑንም ጠቁሟል።

የቻይና ብሄራዊ የሳይንስ ፋውንዴሽን እና ብሄራዊ የምርምር ተቋም ተመራማሪዎች ጥናቱን እድሜያቸው ከ30 እስከ 79 ዓመት መካከል በሆኑ 456 ሺህ 155 ሰዎች ላይ ነው ያካሄዱት።

ተመራማሪዎቹ በጥናቱ ተሳታፊዎች ላይ ለ9 ዓመት ክትትል ያደረጉ ሲሆን፥ የጉሮሮ ካንሰር ተጋላጭነት በምን መልኩ ይጨምራል የሚለውንም ተመልክተወዋል።

በጥናቱ ወቅትም 1 ሺህ 731 የጉሮሮ ካንሰር ህመሞች የተመዘገቡ ሲሆን፥ በጣም የሚያቃጥል ሻይ እና አልኮል አብዝቶ መጠጣት አሊያም ሲጋራ ማጨስ የጉሮሮ ካንሰር ተጋላጭነተን እንደሚጨምርም ተለይቷል።

ሲጋራ አጫሾችም ሆኑ አልኮል የሚጠጡ ሰዎች የሻይ አምሮታቸውን መቁረጥ ከፈለጉ አቀዝቅዘው መጠቀም እንዳለባቸውም ነው ጥናቱ የመከረው።

የጉሮሮ ካንሰር አደገኛ ከሚባሉ ስምንት የካንሰር አይነቶች የሚመደብ ሲሆን፥ በየዓመቱ ከ400 መቶ ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው ህይወታቸው እንደሚያልፍ አለም አቀፉ የካንስር ምርምር ተቋም መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ www.upi.com