የአልኮል ጉዳትን ለመቀነስ በዘርፉ ላይ የሚጣለውን ቀረጥ ከፍ ማድረግ ጠቃሚ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 04፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) የአልኮል ጉዳትን ለመቀነስ በዘርፉ ላይ የሚጣለውን ቀረጥ ከፍ ማድረግ ጠቃሚ መሆኑ ተገልጿል።

የምዕራባዊያን ተመራማሪዎች ከ16 ሀገራት በሰበሰቧቸው መረጃዎች ላይ በአደረጉት ጥናት ከአልኮል ጋር ተያያዥነት ያላቸው በሽታዎችና አደጋዎችን ለመከላከል በአልኮል መጠጦች ላይ ከፍተኛ ቀረጥ መጣል፣ አልኮል የሚሸጥበት ሰዓት ላይ ገደብ ማስቀመጥ እና በአልኮል መጠጥ ላይ የሚሰሩ ማስታወቂያዎችን ስርዓት ማስያዝ ጠቃሚ ነው ተብሏል።

በአለም አዓቀፍ ደረጃ ከሚከሰቱት በሽታዎች 4በመቶ እና ከሚመዘገበው የሰው ልጅ ሞት 5 በመቶ ያህሉ በቀጥታ ከአልኮል ጋር ተያያዥ ያለው መሆኑም ነው የተገለጸው።

በዚህም ከላይ የተጠቀሱ አማረጮቸን ተግባራዊ በማድረግ ብቻ እድሜን ለማራዘም የህክምና ወጭን ለመቀነስ መቻሉን  ነው ዘገባው የሚያስረዳው።

በዘረፉ ላይ ቀረጥ መጨመር ብዙም ተመራጭ ባይሆንም ወጭ ቆጣቢ በሆነ መንገድ በአጭር ጊዜ የዘርፉ አቅርቦት ውስን እንዲሆንና የተጠቃሚዎቸን ቁጥር ለመቀነስ የሚስችል መሆኑን የጥናቱ ተሳታፊ ዳን ቺሾሎም ተናግረዋል።

ከቀረጥ ጭማሬ በተጨማሪ የአልኮል ሽያጭ አገልግሎት ሰዓትን መወሰንና በዘርፉ ላይ የሚሰሩ ማስታወቂያዎች ላይ ገደብ በመጣል ከአልኮል ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ጉዳቶችን ለመከላከል መቻሉም ተጠቁሟል።

ከአልኮል ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ጉዳዮችን በቁጥጥርና ክትትል ለመካለከል የሚያስችሉ ሌሎች አማራጨች ግን ወጭ ቆጣቢና አዋጭ ያለመሆናቸውንም ነው ዘገባው የሚያመላክተው።

 

ምንጭ፥ upi.com

የተተረጎመውና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ