ሩሲያ በሶሪያ ተቃዋሚ ሃይሎች ላይ የመጀመሪያውን የአየር ጥቃት ፈፀመች

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 19 ፣ 2008 ( ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በሶሪያ ተቃዋሚ ሃይሎች ላይ የመጀመሪያውን የአየር ጥቃት መፈፀም ጀመረች።

የአሜሪካ መከላከያ ባለስልጣናት እንዳሉት፥ ጥቃቱ የተፈጸመው በሶሪያዋ ምዕራባዊ ከተማ ሆምስ አካባቢ ነው።

የተጀመረው የሩሲያ የአየር ጥቃት ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ የሩሲያን ወታደራዊ ድጋፍ መጠየቃቸውን ተከትሎ መሆኑን የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

የሩሲያ አየር ሃይል በሶሪያ ለሚያደርገው ዘመቻ ከሃገሪቱ የላይኛው ፓርላማ መተማመኛ ማግኘቱን ከሩሲያ የሚወጡ ሪፖርቶች ያመለክታሉ።

ፅንፈኛው አይ ኤስን ጨምሮ ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች የበሽር አላሳድን መንግስት ከስልጣን ለማውረድ የሚያከሂዱት ውጊያ  አራት አመታትን አስቆጥሯል።

እስካሁንም ከ2 መቶ 50 ሺህ በላይ ሰዎች ሲሞቱ በሚሊየን የሚቆጠሩት ደግሞ ቆስለዋል፤ ከ11 ሚሊየን የሚልቁ ዜጎች ደግሞ ቀያቸውን ለቀው ተሰደዋል።

ምንጭ፥ ቢቢሲ