ዋልያዎቹ በወዳጅነት ጨዋታ ቦትስዋናን 3-2 በሆነ ውጤት አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋልያዎቹ ከቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የወዳጀነት ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በቦትስዋና ጋቦሮኒ በተደረገው የወዳጀነት ጨዋታ ላይ ዋልያዎቹ ሁለቱን ግቦች በመጀመሪያው ግማሽ ያስቆጠሩ ሲሆን፥ ቀሪዋን ግብ በሁተኛው አጋማሽ አስቆጠረዋል።

የቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን በባዶ ከመውጣት የታደጋቸውን ሁለት ግቦች  በሁለተኛው አጋማሽ ማስቆጠር ችለዋል።

የቦትስዋና እግር ኳስ ማህበር ሃገሪቱ የምታከብረውን የነፃነት በአል አስመልክቶ ነው ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በላከው የወዳጅነት ጨዋታ ግብዣ ነው ጨዋጻው የተደረገው።

ጨዋታው ከፊፋ የወዳጅነት ጨዋታ መርሃ ግብር ውጪ በመሆኑም ሳላህዲን ሰዒድ፣ ሽመልስ በቀለ፣ ጌታነህ ከበደ እና ኡመድ ኡኩሪ በቡድኑ ውስጥ አልተካተቱም ነበር።

በ2013 የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋልያዎቹ ቦትስዋናን በጋቦሮኒ በሳላህዲን ሰዒድ እና ጌታነህ ከበደ ጎሎች 2 ለ 1፤ በአዲስ አበባ ደግሞ 1 ለ 0 መርታታቸው  የሚታወስ ነው።

ለ2018ቱ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንስፔ እንዲሁም ለ2016ቱ የአፍሪካ አገሮች እግር ኳስ ዋንጫ /ቻን/ ከቡሩንዲ ጋር ለሚደርገው ጨዋታ ቅድመ

ዝግጅት እንዲያደርጉ በአሰልጣኝ ዮሃንስ የተመረጡት 19 ተጫዋቾች:-

ግብ ጠባቂዎች   

1. ታሪክ ጌትነት      

2. ለዓለም ብርሃኑ      

3. አቤል ማሞ

ተከላካዮች  

1. ስዩም ተስፋዬ  

2. ተካልኝ ደጀኔ  

3. አሰቻለው ታመነ  

4. አንተነህ ተስፋዬ  

5. ሙጂብ ቃሲም          

6.  ዘካርያስ ቱጂ

አማካዮች

1. ኤፍሬም አሻሞ   

2. ጋቶች ፓኖም    

3. ሙሉዓለም መስፍን   

4. ብሩክ ቃልቦሬ   

5. ቢኒያም በላይ    

6. በረከት ይስሃቅ    

7. አስቻለው ግርማ

አጥቂዎች  

1. ባዬ ገዛኸኝ      

2. ዳዊት ፈቃዱ        

3. ራምኬል ሎክ መሆናቸው ይታወሳል።
 

የተጫነው፦ በሙለታ መንገሻ