አሜሪካዊው በ30 ቀናት ውስጥ በእርሱ ምክንያት የተከማቸ ቆሻሻ ለብሶ እንደሚዞር አስታውቋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካዊው ሮብ ግሪንፊልድ በ30 ቀናት ውስጥ በእርሱ ምክንያት ተፈጥረው የተከማቹ ቆሻሻዎችን ለብሶ ለመዞር እንደተዘጋጀ አስታውቋል።

ግለሰቡ ቆሻሻውን በልብስ መልክ በተሰፋ ፕላስቲክ ውስጥ በመጨመር እንደሚለብስ አስታውቋል።

ግለሰቡ ይህንን እንዲያደርግ ያነሳሳው በቆሻሻ አወጋገድ ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሆነም አስታውቋል።

ሮብ ግሪንፊልድ በዚህ ተግባሩም በቀን በሱ ምክንያት የሚፈጠረውን 2 ኪሎ ግራም ቆሻሻ፤ የ30 ቀናት 60 ኪሎግራም የቆሻሻ ነው ለብሱየሶ የሚዞረው።

ሮብ ግሪንፊልድ ይናገራል፥ “ይህን እንዳደርግ ያነሳሳኝ ሰዎች የቆሻሻ አወጋገዳቸውን እንዲያስተካክሉ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው” ብሏል።

“በርካታ ሰዎች በየእለቱ ስለሚፈጥሩት ቆሻሻ አያስቡም” ያለው ግሪንፊልድ፥ አንድ ጊዜ ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ከጣሉት የተወገደ ይመስላቸዋል” ሲል ተናግሯል።

ሆኖም ግን አንድ ሰው በቀን በአማካኝ 2 ኪሎግራም ቆሻሻ የሚፈጥር ከሆነ ይህን ሲጠራቀም በአካባቢ ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ማስላት አያዳግትም ሲልም ተናግሯል።

“አሁን የማደርገው ጉዞ ግን ሰዎች ስለ አካባቢያቸው ትኩረት እንዲሰጡ ግንዛቤ ለመፍጠር እና በቀን ውስጥ የሚፈጥሩትን የቆሻሻ መጠን እንዲቀንሱ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው” ሲልም አስታውቋል።

ሮብ ግሪንፊልድ ቆሻሻውን ለብሶ የሚያደርገው ጉዞም በተለያዩ የሚዲያ ጣቢያዎች እና የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾች የቀጥታ ሽፋን እንደሚሰጠውም ተነግሯል።

ምንጭ፦ www.upi.com/Odd

 


በሙለታ መንገሻ