ቢዝነስ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 7 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከተማ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ።


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ አዲስ የሚገነባውን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ለማስጀመር እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው።

አውሮፕላን ማረፊያውን ለመገንባት የሚያስፈልገውን የቦታ ጥያቄ ለመፍታት ከኦሮሚያ ክልል ጋር ምክክር እየተደረገ መሆኑን አቶ ተወልደ ተናግረዋል።

ሊገነባ የታሰበው ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሁሉንም አገልግሎቶች የሚሰጥ የራሱ ሆቴል ይኖረዋል ተብሏል።

አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ በአመት ከ80 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑንም ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።

በዙፋን ካሳሁን

 

አዲስ አበባ ነሀሴ ፣5፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቻድ አየር መንገድን የ49 በመቶ ድርሻ ሊገዝ መሆኑ ተገለፀ።

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 4 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈረንጆቹ 2017/18 አመት 233 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።


የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፥ አየር መንገዱ በፈረንጆቹ 2017/18 አመት የተጣራ 233 ሚሊየን ዶላር ትርፍ ማግኘቱን ተናግረዋል።

ካለፈው አመት አንጻር የ4 ሚሊየን ዶላር ብልጫ ማሳየቱንም ነው የተናገሩት።

ትርፉ አየር መንገዱ በሰጠው ከ10 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ የመጓጓዣ እና ከ400 ሺህ ቶን በላይ የጭነት አገልግሎት የተገኘ መሆኑንም ገልጸዋል።

በዚህም የአየር መንገዱ አጠቃላይ ገቢ 43 በመቶ እድገት ማሳየቱን ጠቅሰዋል።

የጭነት አገልግሎቱ 18 በመቶ የመንገደኞች ቁጥር ደግሞ 21 በመቶ ዕድገት ማሳየቱንም አስታውቀዋል።

ተጨማሪ 14 አውሮፕላኖችን በማስገባት 10 አዳዲስ መዳረሻዎች መክፈቱንም አንስተዋል።

አሁን ላይም አየር መንገዱ ባሉት ከ100 በላይ አውሮፕላኖች በ115 መዳረሻዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

በዙፋን ካሳሁን

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኖርዌይ ቻይና ቀጥታ የእቃ ጫኝ (ካርጎ) አውሮፕላን በረራ ሊጀምር መሆኑ ተሰምቷል።

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 2፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምግብ መጠጥ እና እና ፋርማሲዩቲካል ዘርፎች በዚህ ዓመት ብቻ ከ45 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የስራ እድል መፈጠሩን የምግብ መጠጥ እና ፋርማሲቲካል ኢንደስትሪዎች ልማት ኢኒስቲትዩት አስታወቀ፡፡