የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ159 ሚሊየን ብር በመርካቶ ያስገነባውን ገዳ ህንፃ አስምረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ159 ሚሊየን ብር በመርካቶ አመዴ ገበያ አካባቢ ያስገነባውን ገዳ ህንፃ ዛሬ አስምረቀ።

የባንኩ 75ኛ ዓመት ክብረ በዓል ፕሮጀክት ፅፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም መኩርያ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ግንባታው ተጠናቆ ዛሬ የተመረቀው ገዳ ህንፃ በርካታ አገልግሎቶች የሚሰጡበት ነው።

ህንፃው የተገነባው የቀድሞው የባንክ ፓውሎስ ቅርጫፍ ያለበት ሲሆን፥ በዘርፉ አዲስ የሆነው የደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግል ተናግርዋል።

አቶ ኤፍሬም ከዚህ በተጨማሪም ባንኩ የወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዋና ክፍሉን በዚያ ህንፃ ውስጥ አደራጅቶ እንዲሰራ ይደረጋል ነው ያሉት።

ገዳ ህንፃ ባለ 11 ወለል ሲሆን፥ ሁለት የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች ያሉት በውስጡ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን ተደርጎ የተገነባ መሆኑን

በስላባት ማናዬ