የነሃሴ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የነሃሴ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ በነሃሴ ወር ከአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በስተቀር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ብሏል።

የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በሐምሌ ወር ይሸጥበት ከነበረው በ0 ነጥብ 42 ሳንቲም ቅናሽ ማሳየቱን ገልጿል፡፡

ሌሎች የነዳጅ ምርቶች በሐምሌ ወር ሲሸጡበት በነበረው ዋጋ እንደሚቀጥሉ የሚኒስቴሩ መግለጫ ያመለክታል።