የተማሪያቸውን ህፃን ልጅ አቅፈው ሙሉ ክፍለ ጊዜ ያስተማሩት ፕሮፌሰር እየተደነቁ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሮፌሰሩ በክፍል ውስጥ የአንዲት ተማሪያቸውን ህፃን ልጅ አቅፈው ሙሉ የትምህርት ክፍለ ጊዜውን ያለምንም መስተጓጎል ማስተማራቸው የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።

በቴክሳስ ኤ ኤንድ ኤም ዩኒቨርሲቲ መምርህሩ ፕሮፌሰር ሄንሪ ሙሶማ፤ ከተማሪዎቻቸው መካከል አንደኛዋ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ለልጇ የሚሆን የህፃን ማስቀመጫ ቦታ ታጣለች።

አሽተን ሮቢንሰን የተባለቸው ተማሪዋ በሜይስ የቢዝነስ ትምህት ቤት ልጇን የምታስቀምጥበት ቦታ በማጣቷ፥ የዕለቱን ትምህርት ልታቋርጠው መወሰኗን ለክፍል መምህሯ ለፕሮፌሰር ሙሶማ ኢሜይል ትልክላቸዋለች።

ሮቢንሰን አስተማሪዋ ፕሮፌሰር ሙሱሟ በላኩላት ምላሽ በጣም ትገረማለች።

ፕሮፌሰሩ የላኩላት ምላሽ “ትምህርቱን በቦታ ማጣት ምክንያት አታቋርጭም፤ እባክሽን ልጅሽን እኔ እይዝልሻለሁ” የሚል ነው።

ተማሪነት እና እናትነትን በአንድ እያስቀጠለች የምትገኘው ሮቢንሰን በፌስቡክ ገጿ ባጋራችው ቪዲዮም፥ ፕሮፌሰሩ ህጻን ኤመትን አቅፈው ያለምንም ችግር ትምህርት ሲሰጡ ታይተዋል።

እናትነት እና ተማሪነት ብዙ ሃላፊነትን ቢጥልብሽም ፕሮፌሰር ሄንሪ ሙሶማ ግን ሁሉም ነገር ቀላል መሆኑን በትናንቱ ውለታቸው የህይወት ትምህርት ሰጥተውኛል ብላለች።

ኤመት ሲያድግም አንተን እያሳደግሁ ትምህርቴን አጠነቀቅቄ በዓለም ታዋቂ ከሆነ ዩኒቨርሲቲ ተመርቂያለሁ ብዬ እንደምነግረውና የፕሮፌሰርን ውለታ እንደማጫውተው ተስፋ አለኝ ብላለች።

የፕሮፌሰር ሙሶማ ያልተለመደ ዓይነት ድርጊት የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ሚኬል ኬ ዮንግን ጨምሮ ብዙዎችነ አስደንቋል።

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ ዩናይትድ ፕረስ ኢንተርናሽናል