የዓለማችን ወፍራሟ ሴት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ኤማን አህመድ አብድ ኤል አቲ የምትባለውና የዓለማችን ወፍራሟ ግብፃዊት ሴት ዩናይትድ ዓረብ ኢምሬትስ ውስጥ ህይወቷ አልፏል።

ኤማን በተያዘው የፈረንጆቹ አመት መጀመሪያ አካባቢ ወደ ህንድ በማቅናት የቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጎላት ነበር።

በወቅቱ 500 ኪሎ ግራም ትመዝን የነበረችው ኤማን በቀዶ ጥገና ህክምናው፥ እስከ 300 ኪሎ ግራም ቀንሳ ነበር ተብሏል።

ሆኖም ዛሬ በተሰማው ዜና የዓለማችን ወፍራሟ ሴት በሌላ የጤና ችግር ህይወቷን አጥታለች።

ለኤማን ህክምና ሲያደርግላት የቆየው ሆስፒታል ያወጣው መረጃ፥ የ37 ዓመቷ ወፍራም ሴት የልብ ህመም እና የኩላሊት ችግር እንደነበረባት ያስረዳል።

ሆስፒታሉ በህልፈተ ህይወቷ የተሰማውን ልባዊ ሀዘንም ለቤተቦቿ ገልጿል።

ኤማን አብድ ኤል አቲ ከህንድ በተፃፈላት የተሻለ ቀዶ ህክምና ትዕዛዝ መሰረት ከግንቦት ወር ጀምሮ በዩናይትድ ዓረብ ኢምሬትስ ዋና ከተማ አቡ ዳቢ ነበር ያሳለፈችው።

የወፍሯሟ ሴት ቤተሰቦች እንደተናገሩት ለቀዶ ህክምና ወደ ሌላ ሀገር ከመሄዷ በፊት ለ25 ዓመታት ከቤት ወጥታ አታውቅም።

እህቷ በቀጥታ ኢንተርኔት ባደረገችው የድጋፍ ቅስቀሳ አማካኝነት ቀዶ ህክምና ለማድረግ ወደ ህንድ ሙምባይ ብትጓዝም፥ ቤተሰቦቿ የቀዶ ጥገና ህክምናውን በሚሰጡት ሃኪሞች ስላልተደሰቱ ወደ አቡ ዳቢ እንዲሄዱ ተደረጉ።

ሆኖም ኤማን አብድ ኤል አቲ ዛሬ ህይወቷ አልፈፏል።

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ቢቢሲ