ሀርለም ግሎብትሮተርስ በ1 ሰዓት 348 የቅርጫት ኳሶችን ከርቀት ወርውሮ በማስቆጠር አዲስ ክብረ ወሰን ያዘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሀርለም ግሎብትሮተርስ የተባለ የአሜሪካ የቅርጫት ኳስ ቡድን በ1 ሰዓት 348 የቅርጫት ኳሶችን ከርቀት ወርውሮ በማስገባት አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ያዘ።

ስድስት የቅርጫት ኳስ ቡድኑ አባላት ከግማሽ ሜዳ በመወርወር በርካታ ቅርጫቶችን በአንድ ሰዓት ውስጥ ማስቆጠር በሚል ነው ክብረ ወሰኑን በእጃቸው ያስገቡት።

ሀርለም ግሎብትሮተርስ የቅርጫት ኳስ ቡድን በአንድ ሰዓት ውስጥ 348 የቅርጫቶችን ማስቆጠር መቻላቸውም ተነግሯል።

የቅርጫት ኳስ ቡድኑ አባላት በሰጡት አስተያየት፥ በርትተን በመስራታችን ለዚህ ክብር በቅተናል፤ በዚህም ደስተኞች ነን ብለዋል።

“እዚህ ስኬት ላይ ለመድረስም ብዙ ሰርተናል” ብለዋል።

ምንጭ፦ www.upi.com/Odd