የ11 ሺህ ዶላር ዝርዝር ሳንቲም ይዞ መኪና ለመግዛት ያመራው ግለሰብ ለቆጠራ የመኪና መሸጫውን አዘግቷል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይና የሚገኝ አንድ መኪና መሸጫ ደንበኛቸው መኪና ለመግዛት በርካታ ዝርዝር ሳንቲሞችን ይዞ በመምጣቱ ለቆጠራ ሲል ሌሎች ስራዎችን ማቆሙ ተነግሯል።

የመኪና መሸጫ ኩባንያው ግለሰቡ ይዞት የመጣውን የ11 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ ዝርዝ ሳንቲሞችን ለመቁጠር በሚል ነው የእለቱ ስራውን በማቋረጥ ሱቁን የዘጋው።

ታህሳስ 8 ቀን የተቀረፀ ቪዲዮ እንደሚያመለክተው በቻይና ፉጂያን ግዛት ፑቲያን ከተማ የሚገኝ የቢ.ኤም.ደብሊው ተሽከርካሪ መሸጫ ሰራተኞች በ10 ትላልቅ ሳጥኖች ውስጥ ሆነው የመጡትን ሳንቲሞች ሲቆጥሩ ውለዋል።

ሳንቲሞቹንም መኪና መግዛት የሚፈልግ ሰው ይዟቸው እንደመጣ ነው ሰራተኞቹ የተናገሩት።

ግለሰቡ ለመኪና መሸጫው ሰራተኞች እንደተናገረው፥ ሳንቲሞቹን መኪና ለመግዛት በሚል ሲያጠራቅማቸው እንደነበረ እና አሁን ላይ ሊገዛለት በመቻሉ ይዞት ሄዷል።

ምንጭ፦ www.upi.com/Odd