በእስራኤል ተመራማሪዎች የበለፀገው በዓለም በመጠኑ ትንሽ የሆነው ቲማቲም ብዙዎችን አስደምሟል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) በእስራኤል ተመራማሪዎች የበለፀገው በዓለም በመጠኑ ትንሽ የሚባል ቲማቲም የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።

የእስራኤል ኩባንያ የሆነው ኬድማ በሀገሪቱ በእርሻ ስፍራ ውስጥ በዓለም በመጠን ትንሽ የሚባል ቲማቲም ማበልፀጉን አስታወቋል።

ቲማቲሙ በቀይ እና ቢጫ ቀለማት እንደበለፀገ ነው የተነገረው።

ቲማቲሙ ከዚህ በፊት ከምናውቃቸው መደበኛ መጠን ያላቸው ቲማቲሞች ይልቅ ጣፋጭ መሆኑም ነው የተገለፀው።

በእስራኤል ደቡባዊው አቨቫ በረሃማ ምድር በሚገኘው ኬድማ ኩባንያ ውስጥ የአትክልት አብቃይ የሆነው አሬል ኪድሮን፥ አዲሱ ቲማቲም ከመደበኛው ቲማቲም 30 በመቶ የሚበልጥ ጥፍጥና እንዳለው ገልፀዋል።

zkc_2018-01-04_13-45-06_199.jpg

የአዲሱ ቲማቲም ዝርያ ዘር በመጀመሪያ የበለፀገው ሆላንድ ውስጥ ሲሆን፥ ከዚያ በኋላ በክልሉ ካለው ደረቅ ሁኔታ ጋር ለማጣጣም በሚያስችል መልኩ መሻሻሉም ተነግሯል።

አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት አዲሱ የቲማቲም ዓይነት በጣም ብዙ አዲስ የምግብ አዘገጃጀቶች ያመጣል ተብሎ ይታመናል።

በዚህም መጠኑ ምቹ፣ ጣእሙ የተመጣጠነ በመሆኑ፥ ምግብ በማብሰል እና በመመገብ መልካም ባህሪ እንዳለው ነው የተገለፀው።


ምንጭ፦ ሲ.ጂ.ቲ.ኤን.