ሶስቴ ለመደገስ አቅም የለኝም ያለው ሰው በአንድ የሰርግ ስነ ሰርዓት ሶስት ሚስቶችን አግብቷል

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) ሶስት ሚስቶችን ለማግባት ሲሰናዳ የኖረው ሰው የተለያዩ ሰርጎችን የመደገስ አቅም የለኝም በሚል በአንድ የሰርግ ስነ ስርዓት ሶስት ሚስቶችን አግብቷል።

የ50 ዓመት ዕድሜ ያለው ኡጋንዳዊው መሃመድ ሰማንዳ፥ በፈፀመመው ተግባር የአፍሪካን መገናኛ ብዙሃን ቀልብ ስቧል ነው የተባለው።

ሰማንዳ ሶስቱን ሴቶች ለማግባት ቢፈልግም፥ ለእያንዳንዷ ሴት በተለያዩ ጊዜያት ሰርግ የመደገስ አቅም የለኝም ሲል ተናግሯል።

ሰማንዳ በኡጋንዳ ዋኪሶ ግዛት ነዋሪ ሲሆን፥ ምግብ በመሸጥ የሚተዳደር ነው።

የ50 ዓመቱ ሰው ያገባቸው ሶስቱም ሴቶች ምንም ዓይነት ቅናት እንደሌለባቸው የገለፀ ሲሆን፥ ኑሯቸውን ለመደገፍ ጠንክሮ እንደሚሰራ ነው የተናገረው።

 

ምንጭ፦ www.odditycentral.com