ልጆች የመውለድ ሱስ የተጠናወታቸው እህትማማቾች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለአንዳንድ እናቶች ልጅ አብዝቶ መውለድ አድካሚ እና አስቸጋሪ የሚሆንባቸው ሲሆን፥ ለእህትማማቾቹ ኤሚ እና ኮል ግን ይህ ፈፅሞ የማይታሰብ ነው።

የ31 እና 29 እድሜ ያላቸው እህትማማቾቹ እያንዳንዳቸው እስካሁን ስምንት ስመንት ልጆች መውለዳቸውን ነው የሚናገሩት።

ልጆች የመውለድ ሱስ ተጠናውቶናል የሚሉት እህትማማቾቹ፥ አንድኛዋ ከባሏ ጋር የፍቺ ፈፅማ የተለያየች ቢሆንም ከእሱ ግን አሁንም ልጅ እየወለደች መሆኑን ነው የምትናገረው።

16_n.jpg

የ31 ዓመቷ ኤሚ እና የ29 ዓመቷ ኮል በዌልስ የሚገኝ ገዋየንድ በሚባል ገጠራማ አካባቢ የሚኖሩ ሲሆን፥ የመኖሪያ ቤታቸው መካከል ያለው ርቀትም የ5 ደቂቃ ብቻ ነው።

አንድ ላይ 16 ልጆች ያላቸው እህትማማቾቹ ገበያ ከመሄድ ጀምሮ የልጆችን መገብ ማዘጋጀት እና ሌሎችንም ስራዎች እንደ ላይ እንደሚያከናውኑ ነው የሚናገሩት።

ኤሚ ትናገራለች፥ “የመጀመሪያ ሁለት ልጆቼን ከወለድኩ በኋላ ልጆች መውለድን በጣም እየወደድኩ መጣሁ፤ አሁንም ልጅ መውለድን ማቆም አልፈልግም” ብላለች።

ከእህቷ ጋር በጣም እንደትምቀራረብ የምትናገረው ኤሚ፥ ልጆቻቸውም በጣም ጓደኛሞች መሆናቸውን ነው የምትናገረው።

እህትማማቾቹ አሁንም ቢሆን ልጅ የመውለድ ፍላጎት እንዳላቸውም ኤሚ አስታውቃለች።

ምንጭ፦ www.thesun.co.uk