በፓሪስ ባቡር ጣቢያ ውስጥ በተሳሳተ አቅጣጫ የተጓዘችው ሴት ገንዘብ ተቀጥታለች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፓሪስ ከተማ ባቡር ጣቢያ ውስጥ በተሳሳት አቅጣጫ የተጓዘችው ነብሰ ጡር ሴት በባቡር ጣቢያው የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለበት ተሰምቷል።

ግለሰቧ በተከለከለ አቅጣጫ በመጓዟም 60 ዩሮ መቀጣቷ ነው የተነገረው።

ግለሰቧ የእግር ጉዞዋን ለማሳጠር ብላ ነበር አቋራጭ ለመጠቀም የተሳሳት አቅጣጫን የተጠቀመቸው።

ሆኖም ግን ይህንን ተግባሯን የተመለከተ የባቡር ጣቢያው ሰራተኛ ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ የ60 ዩሮ ቅጣት ትኬት አንደቆረጠባት ታውቋል።

የፓሪስ ከተማ ባቡር ጣቢያ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት፥ ባቡር ጣቢያው ባልተፈቀደ መንገድ የሚጓዙ ሰዎች ላይ ቅጣይ ይጥላል።

በግለሰቦች ላይ ቅጣት ለመጣል ማስጠንቀቂያ የመስጠት ግዴታ የለብንም ያሉት ቃል አቀባዩ፥ ምክንያቱ ደግሞ ቀድሞ ምልክቶች ስለተቀመጡ ነው ብለዋል።

ሰዎች በተፈቀደላቸው እና በአንድ አቅጣጫ ብቻ አንዲጓዙ የተደረገውም የሰዎች እርስ በእርስ እንዳይገፋፉ እና እንዳይጋጩ ነው ያሉ ሲሆን፥ ከዚህ በተጨማሪም የሰዎች የመመላለስ ፍሰት ከመጨናነቅ የፀዳ እንዲሆን ለማድረግ ነው ብለዋል።

ምንጭ፦ www.ndtv.com