የቴክሳስ የኬክ ቡድን ከ91 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝነው ግዙፍ ኬክ በመስራት የአለም ክብረወሰን ለመስበር ተዘጋጅቷል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የቴክሳስ የኬክ ቡድን በሀገሪቱ ዋና ከተማ ኡስቲን በሚካሄደው 19ኛው አመታዊ የውሾች የእግር ጉዞ ቀን ላይ በአለም ግዙፍ የሚባለው ኬክ በማዘጋጀት ስማቸው በድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ለማስፈር ተዘጋጅቷል።

የዓለም ክብረ ወሰን ለመስበርም የሚሰራው ኬክ ክብደት ከ91 ነጥብ 7 ኪሎ ግራም በላይ መመዘን እንዳለበት ተገልጿል።

ግዙፉ ኬክ ለትርፍ ያልተቋቋመው የውሻ አገልግሎት ድርጅት በፈረንጆቹ የፊታችን መጋቢት 24 ለህዝብ እይታ ይፋ የሚያደርገው ሲሆን፥ ይህም ኬኩ ሁሉም ተወዳዳሪ ውሾች በተገኙበት ይቀርባል።

ታላቁ የቴክሳስ ውሾች የእግር ጉዞ ለሰባኛ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን፥ በዚህ ታላቁ የቴክሳስ ውሾች የእግር ጉዞ ላይ ከሐኪሞች እና አሰልጣኞች ነፃ የምክር አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል።

በሌላ በኩል የኬክ ሰሪ ባለሙያዎች ቡድን በአካባቢያቸው በሚገኝ ምግብ ቤት ውስጥ አነስተኛ የሚባለው ጣፋጭ ኬክ ለመስራት እየተዘጋጁ ነው።

www.upi.com