ኦባማ ቶክ ሾው ለማዘጋጀት ከኔትፍሊክስ ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከኢንተርኔት መዝናኛ ኩባንያው ኔትፍሊክስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ቶክሾው ለማዘጋጀት ውይይት ላይ እንደሚገኙ ኒውርክ ታምስ ዘግቧል።

ፕሮግራሙ የሕዝብን ትኩረት ይስባሉ በሚባሉ አገራዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚያጠነጥን ተገልጿል።

ክፍያውን በተመለከተ በሚገቡት ውል መሰረት ኔትፍሊክስ ለኦባማና የቪዲዮ ይዘቱን ለሚከታተሉት ለቀድሞ ቀዳማዊ እመቤት ሚሼል ኦባማ ክፍያ እንደሚፈጽም ተገልጿል።

በተያያዘ ስለክፍያ መጠኑና በመካከላቸው ስለተደረሰው ስምምነት እስካሁን በይፋ የተገለጸ ነገር የለም።

ኦባማ የሚያቀርቡትን ቶክሾው ፕሬዝዳንት ትራምፕንና ወግ አጥባቂዎችን ለማጥቃት እንደማይገለገሉበት ተጠቅሷል።

ከኔትፍሊክስ በተጨማሪ አማዞንና አፕል በይዘት ጉዳይ ላይ ለመወያየት ፍላጎት ማሳየታቸውን ተነግሯል።

ባለፈው ዓመት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ሚሞር በመባል የሚታወቀውን የቤተመንግስት ትዝታቸውን በ60 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መሸጣቸው የሚታወስ ነው፡፡

 

 

 


ምንጭ፦ ሮይተርስ
ተተርጉሞየተጫነው፦ በአብረሃምፈቀደ