ቅዱስ ጊዮርጊስ ፖርቹጋላዊው ማኑኤል ቫዝ ፒንቶን አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስ ፖርቹጋላዊው ካርሎስ ማኑዌል ቫዝ ፒንቶ አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙ ተነግሯል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ የስፖርት ማህበር እና ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ካርሎስ ማኑዌል ቫዝ ፒንቶ መካከልም ለሁለት ዓመት የሚቆይ ኮንትራትም ተፈራርመዋል። 

የ43 ዓመቱ አስልጣኝ የካፍ እና የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበራት ህብረት የአስልጣኝነት ኤ ላይሰንስ ያላቸው ሲሆን፥ የአንጎላውን ሪክሬቲቮ ሊቦሎ ክለብ በማሰልጠን ላይ ነበሩ።

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ካርሎስ ማኑዌል ቫዝ ፒንቶ ከአንጎላውን ሪክሬቲቮ ሊቦሎ ክለብ በነበራቸው ቆይታ ያስመዘገቡት ትልቁ ስኬት ክለቡ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የምደብ ድልድል ውስጥ እንዲገባ ማድረግ ነው።

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ካርሎስ ማኑዌል ቫዝ ፒንቶ ለቀጣይ ሁለት አመታት ከፈረሰኞቹ ጋር የሚቆዩ ይሆናል።

ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ያሳለፉት አሰልጣኝ ማርት ኑይ በጤና እክል ምክንያት ከክለቡ የእለት ተእለት ስራ ከተገለሉ ከ4 ወራት በኋላ ነው ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ አሰልጣኝ የሾመው።