በፕሪምየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና ድል ሲቀናው ሌሎች ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 3ኛ ሳምንት እና በብሄራዊ ቡድን ጨዋታ ምክንያት ያልተሄደ የ1ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ተካሂደዋል።

በብሄራዊ ቡድን ጨዋታ ምክንያት ያልተሄደው የ1ኛ ሳምንት ጨዋታም በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ቡና እና በመከላከያ መካከል ነው የተካሄደው።

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው የኢትዮጵያ ቡና እና የመከላከያ ጨዋታም በኢትዮጵያ ቡና 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በጨዋታው ላይም ሳሙኤል ሳኑሚ በ84ኛው ደቂቃ ላይ ብቸኛዋን የኢትዮጵያ ቡና የማሸነፊያ ጎል ከመረብ አሳርፏል።

በዛሬው እለት በተካሄዱ የ3ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ደግሞ ወልዲያ ከተማን ከድሬ ዳዋ እንዲሁም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን ከሲዳማ ቡና አገናኝቷል።

ወልዲያላይ የተካሄደው የወልዲያ ከተማ እና የድሬ ደዋ ከተማ ጨዋታም ያለ ምንም ጎል 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

በተመሳሳይ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን ከሲዳማ ቡና ጨዋታም ያለ ምንም ጎል 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ነው የተጠናቀቀው።

የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች በነገው እለትም ቀጥለው የኪሄዱ ሲሆን፥ ጅማ አባ ጅፋር ከፋሲል ከተማ፣ አርባምንጭ ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ደደቢት ከሀዋሳ ከተማ፣ ወላይታ ድቻ ከአዳማ ከተማ እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመቐለ ከተማ ይጫወታሉ።