በፕሪሚየር ሊጉ አዳማ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 3 ለ 2 አሸንፏል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ)ዛሬ በተደረገው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከአዳማ ከተማ አዲስ አበባ ስተድየም ላይ ተገናኝተዋል።

በጨዋታውም አዳማ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ለአዳማ ከተማ ቡልቻ ሹራ አንድ ግብ፣ ዳዋ ሆቴሳ ሁለት ግብ ለቡዱናቸው ሲያስቆጥሩ፥ ዳዋ ሆቴሳ ካስቆጠራቸው ግቦች አንዱ በቅጣት ምት የተገኘ ነው።

 

በኢትዮ ኤሌክትሪክ በኩል አልሀሰን ካሉሻ እና አዲስ ነጋሽ ግቦችን አስቆጥረዋል።