የ9ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ውጤቶች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ስታዲየሞች ቀጥለው ተካሂደዋል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና እና ከወላይታ ድቻ ተገናኝተዋል።

ጨዋታውም 1ለ1 አቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ በጨዋታው ዳግም በቀለ በ72ኛው ደቂቃ ላይ የወላይታ ድቻን ጎል ሲያስቆጥር፤ የወላይታ ድቻው ተክሉ በላይ በራሱ መረብ ላይ በ61ኛ ደቂቃ ለኢትዮጵያ ቡና አስቆጥሯል።

አዲስ አበባ ላይ የተካሄደው ላሌላኛው ጨዋታ ደግሞ መከላከያ እና ፋሲል ከነማን አገናኝቷል።

ጨዋታውንም ፋሲል ከተማ 1ለ0 በሆነ ውጤት መከላከያን የረታ ሲሆን፥ ራም ኬሎክ በ21ኛው ደቂቃ ላይ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ጎል ለፋሲል ከነማ አስቆጥሯል።

በክልል ላይ በተደረጉ ጨዋታዎችም ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡና ከሀዋሳ ከተማ የተጫወቱ ሲሆን፥ ጨዋታውም በሲዳማ ቡና አሸናፊነት ተጠናቋል።

ጨዋታውን ሲዳማ ቡና 1ለ0 ያሸነ ሲሆን፥ በጨዋታው ላይም አዲስ ግደይ በ90ኛው ደቂቃ የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ጎል ከመረብ አሳርፏል።

መቀሌ ላይ የተደረገው የመቀሌ ከተማ እና የድሬደዋ ከተማ ጨዋታም ባበለሜዳዎቹ መቀሌ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል።

በጨዋታው መቀሌ ከተማ ድሬ ዳዋ ከተማን 2ለ0 የረታ ሲሆን፥ በመጨዋታው ላይም ጋይሳ ኦፖንግ በ36ኛው ደቂቃ እንዲሁም አማኑኤል ገብረ ሚካኤል በ37ኛው ደቂቃ የመቀሌ ከተማን የማሸነፊያ ጎሎች ከመረብ አሳርፏል።

አርባ ምንጭ ላይ የተካሄደው የአርባ ምንጭ ከተማ እና የደደቢት ጨዋታም በደደቢት 2ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

የደደቢትን የማሸነፊያ ጎሎች ጌታነህ ከበደ በ33ኛው እና በ43ኛው ደቂቃ ከመረብ ያሳረፈ ሲሆን፥ የአርባ ምንጭ ከተማን ብቸኛ ጎል ወንድሜነህ ዘሪሁን በ83ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል።

በትናንትናው እለት በተካሄደው የ9ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከአዳማ ከተማ የተጫወቱ ሲሆን፥ ጨዋታውንም አዳማ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2ለ3 በሆነ ውጤት አሸንፏል።