በፕሪምየር ሊጉ መቐለ ከተማና ኢትዮጵያ ቡና አቻ ተለያይተዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ጨዋታዎች ዛሬ መካሄድ ጀምረዋል።

በፕሪምየር ሊጉ 15ኛ ሳምንት ዛሬ አንድ ጨዋታ የተደረገ ሲሆን፥ ጨዋታውም መቐለ ከተማ ና ኢትዮጵያ ቡናን በመቐለ ስታዲየም አገናኝቷል።

ጨዋታውም ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ነው የተጠናቀቀው።

15ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ጨዋታዎች እሁድ እና ሰኞ በክልል እና በአዲስ አበባ ስታዲየም ቀጥለ የሚካሄዱ ይሆናል።

በዚህም መሰረት እሁድ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ፥

አዳማ ከተማ ከጅማ አባጅፋር- በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም

ሲዳማ ቡና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ- በይርጋለም ስታዲየም

ድሬደዋ ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ- በድሬደዋ ስታዲየም የሚጫወቱ ይሆናል።

ሰኞ የካቲት 5 2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 15ኛ ሳምንት አንድ ጨዋታ የሚካሄድ ሲሆን፥ ደደቢት እና መከላከያን ከቀኑ በ11 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ያገናኛል።

ወላይታ ድቻን ከወልዲያ እንዲሁም ሀዋሳ ከተማን ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያገናኘው የ15ኛ ሳምንት ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፏል።