በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) 15ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ክልል ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ቀጥሎ ተካሂዷል።

አዳማ ላይ አዳማ ከተማ ከጅማ አባ ጅፋር ተጫውተዋል።

ጨዋታው አንድ አቻ ሲጠናቀቅ ዳዋ ሆቴሳ ለአዳማ ይሁን እንዳሻው ደግሞ ለጅማ አባ ጅፋር ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ይርጋለም ላይ ደግሞ ሲዳማ ቡና ኢትዮ ኤሌክትሪክን አስተናግዶ አንድ አቻ ተለያይቷል።

ባዬ ገዛኸኝ ሲዳማ ቡናን ቀዳሚ ሲያደርግ ተክሉ ተስፋዬ ደግሞ ኢትዮ ኤሌክትሪክን አቻ ማድረግ ችሏል።

ጎንደር ላይ አርባ ምንጭ ከተማን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ 1 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።

የድል ጎሏንም መሃመድ ናስር በመጀመሪያው አጋማሽ አስቆጥሯል።

ድሬዳዋ ላይ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ ደግሞ በአትራም ኩዋሜና መሃመድ ጀማል ጎሎች 2 ለ 0 አሸንፏል።

ሊጉ ነገም ቀጥሎ ሲካሄድ ደደቢት ከመከላከያ ምሸት 11 ሰዓት ይጫወታሉ።

 

 

ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ