በ17ኛው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 9 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በእንግሊዝ በርሚንግሃም ለሚካሄደው 17ኛው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶችን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ መሰረት በ800 ሜትር ወንዶች አትሌት መሃመድ አማን ብቸኛ ተወዳዳሪ ይሆናል።

ሃብታም አለሙ ደግሞ በሴቶች ሃገሯን ትወክላለች።

በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር፥ ሳሙኤል ተፈራና አማን ወጤ ተወዳዳሪ ይሆናሉ።

በሴቶች ደግሞ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ፣ ዳዊት ስዩምና ጉዳፍ ፀጋዬ ተወዳዳሪዎች ናቸው።

በ3 ሺህ ሜትር ደግሞ በወንዶች ሰለሞን ባረጋ፣ ሃጎስ ገብረህይዎት እና ዮሚፍ ቀጀልቻ በበርሚንግሃሙ ውድድር ኢትዮጵያን ይወክላሉ።

በሴቶች ደግሞ ገንዘቤ ዲባባ፣ ዳዊት ስዩምና ፋንቱ ወርቁ እንደሚካፈሉ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ውድድሩ ከየካቲት 22 እስከ እስከ 25 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ ይሆናል።