ኢትዮጵያ ቡና 7ኛውን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የእግር ኳስ ዋንጫ አነሳ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 7ኛው የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የእግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል።

የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የእግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ ዛሬ ኢትዮጵያ ቡና ከሲዳማ ቡና ባደረጉት ጨዋታ ነው የተጠናቀቀው።

ጨዋታውም በኢትዮጵያ ቡና 2ለ1 አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ የ7ኛው የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የእግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ አሸናፊ መሆን ችሏል።

በኢትዮጵያ ቡና እስካሁን ከተካሔዱት የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የእግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ ላይ የዛሬን ጨምሮ አ4ኛ ጊዜ አሸናፊ መሆን ችሏል።

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ዛሬ ተካሂዷል።

በዛሬው እለት ሶዶ ላይ የተካሄደው ጨዋታ ወላይታ ድቻን ከወልድያ ከተማ ያገናኘ ሲሆን፥ ጨዋታውም በወላይታ ድቻ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የወላይታ ድቻ ግቦችን አምረላ ደልታታ በ65ኛው ደቂቃ እንዲሁም ሁለተኛውን ግብ ደግሞ ጃኮ አራፋት በ90ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል።