ስፔን ለሩሲያው የአለም ዋንጫ የ23 ተጫዋቾችን ዝርዝር ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ዩለን ሎፔቴጉይ በሩሲያው የአለም ዋንጫ ስፔንን የሚወክሉ 23 ተጫዋቾችን ይፋ አድርገዋል።

አሰልጣኙ ሴስክ ፋብሪጋስ፣ አልቫሮ ሞራታ፣ ሁዋን ማታ፣ ማርኮስ አሎንሶን እና አንደር ሄሬራን ከስብስቡ ውጭ አድርገዋል።

ግብ ጠባቂዎች፦ ዴቪድ ዴ ሂያ (ማንቼስተር ዩናይትድ)፣ ኬፓ አሪዛባላጋ (አትሌቲክ ቢልባኦ) እንዲሁም ፔፔ ሬይናን ከናፖሊ ጠርተዋል።

ተከላካዮች፦ ጀራርድ ፒኬ እና ዮርዲ አልባ (ባርሴሎና)፣ ሰርጅዮ ራሞስ፣ ናቾ እንዲሁም ዳኒ ካርቫሃል (ሪያል ማድሪድ)፣ ሴዛር አዝፒሊኩየታ (ቼልሲ)፣ አልቫሮ ኦድሪዮዞላ (ሪያል ሶሲየዳድ) እንዲሁም ናቾ ሞንሪያል ከአርሰናል ተመርጠዋል።

አማካዮች፦ ሰርጅዮ ቡስኬትስ እና አንድሬስ ኢኒዬስታ (ባርሴሎና)፣ ኮኬ እና ሳውል ኒጉየዝ (አትሌቲኮ ማድሪድ)፣ ኢስኮ እና ማርኮ አሴንሲዮ (ሪያል ማድሪድ)፣ ቲያጎ አልካንትራ (ባየርሙኒክ) እንዲሁም ዴቪድ ሲልቫ (ማንቼስተር ሲቲ) ተጠርተዋል።

አጥቂዎች፦ ኢያጎ አስፓስ (ሴልታ ቪጎ)፣ ሮድሪጎ (ቫሌንሺያ)፣ ዲያጎ ኮስታ (አትሌቲኮ ማድሪድ) እንዲሁም ሉካስ ቫዝኩየዝ (ሪያል ማድሪድ) ለሩሲያው የአለም ዋንጫ በቡድኑ ተካተዋል።