ዜናዎች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2010፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ)የቀድሞ የዚንባቡዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ሀገሪቱ በስርቆት አጥታለች በተባለው የአልማዝ ማዕድን ዙሪያ በሀገሪቱ ፓርላማ ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበላቸው።

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ማምሻውን ባህርዳር ከተማ ገብተዋል።

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጎንደር ከተማ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2010፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) አዲሱ የአመራር ምደባ አገራዊ ለውጥ ከዳር ለማድረስ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት የኤፌድሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ።


ሀገሪቱን ከድህነት እና ኋላቀርነት ለማላቀቅ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ምደባው ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

አመራሩ ሀገሪቱ ያላትን እውቀት፣ ሃብትና ጉልበት አስተባብሮ ወደ ተያዘው ግብ ለማድረስ አመራሩ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት አስታውቀዋል።

ለዚህም መንግሥት ህዝብን በሰላም በልማትና በዴሞክራሲ ዙሪያ በማሰባሰብ እና በማነሳሳት ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ማለታቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል፡፡

ይህ ምደባ የአፈጻጸም ውጤትን፣ የማስፈጸም ብቃትን እና የሥራ ልምድን መሠረት በማድረግ የተካሄደው እንደሆነም ገልፀዋል።

እንዲሁም የመንግሥትን የማስፈጸም አቅም በማሻሻል ህዝብ በየደረጃው ለሚያነሳቸው የልማት፣ የዴሞክራሲ፣ የፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ዓላማ ያደረገ እንደሆነም አንስተዋል።

እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ እርምጃው የግልጸኝነት እና የተጠያቂነት አሠራርን በማስፈን መንግሥት ህገ መንግሥታዊ ግዴታውን ለመወጣት ያለውን ቁርጠኝነት እና ተነሳሽነት የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል።

የሀገሪቱን ሀብት ከምዝበራ፣ብክነት በመከላከል ድህነትን እና ኋላቀርነትን ለማሸነፍ አዲሱ አመራር እንደሚሰራ የገለፁ ሲሆን፥ የመልካም አስተዳደር ማነቆ የሆኑ አሠራሮችን ለመፍታት መንግስት ትኩረት አድርጎ እንደሚንቀሳቀስም አስታውቀዋል፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2010፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሮማንያ በቴላቪቭ የሚገኘውን ኤምባሲ ዋን ወደ እየሩሳሌም እንደምታዘዋውር አስታወቀች።