ዜናዎች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በየመን ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሚሊሻዎች ስድስት የፖሊስ አባላትንና ሶስት የመንግስት ወታደሮችን ገደሉ።
ታጣቂ ሚሊሻዎቹ ጥቃቱን ያደረሱት በየመን ደቡባዊ ግዛት በሆነችዋ በአብያን ግዛት ነው።

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የስራ ፈቃድ ሳይኖራቸውና የዘርፉን መስፈርት ሳያሟሉ የጨረር አገልግሎት ሲሰጡ በተገኙ የህክምና ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን አስታወቀ።

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ የአባይ ውሃን በፍትሃዊነት ለመጠቀም ቁርጠኛ አቋም አላት አሉ የኢፌድሪ ውሃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር አቶ አለማየሁ ተገኑ።

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የአፍሪካ ሕብረት የኢቦላ ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ጥረት ላይ ሀገራት ተጨማሪ በጎ ፍቃደኞችን ቫይረሱ ወደ ታየባቸው የምእራብ አፍሪካ ሀገራት እንዲልኩ ጥሪ አቀረበ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 6፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የአንድ ድልድይ ግንባታና የሁለት መንገዶች ዲዛይን ስራ ከተቋራጮች ጋር ተፈራረመ።