በግብፅ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የሞቱ ወታደሮችና ፖሊሶች ቁጥር ከ50 በላይ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2010 (ኤፍ. ቢ. ሲ.) በምእራባዊ ግብፅ ታጣቂዎች ድንገት በከፈቱት ጥቃት ከ50 በላይ ወታደሮች እና ፖሊሶች መሞታቸው ተነገረ።

ወታደሮቹ እና ፖሊሶቹ እነዚህን ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ወደስፍራው በማምራት ላይ ነበሩ ተብሏል።

ይሁን እንጂ የፀጥታ ኃይሎቹ ወደ ታጣቂዎቹ መሸሸጊያ ሲቃረቡ በከፈቱት ተኩስ በርካታ ወታደሮችን እና ፖሊሶችን እንደገደሉ እና እንዳቆሰሉ ተመልክቷል።

የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ቁጥራቸውን ባይገልፅም በወቅቱ በነበረው ግጭት የተገደሉ ታጣቂዎች አሉ።

የሽብር ብዱን አባላት፥ በአል-ዋሃት አከባቢ ጊዛ በረሃ ላይ መሽገው ጥቃት ሲያደርሱ ቆይተዋል።

 

 

ምንጭ፦ ሲ.ጂ.ቲ.ኤን