በኦሮሚያ ክልል በህገ ወጥ መንገድ በማእድን ዘርፍ የተሰማሩ 121 ባለሀብቶች ፍቃድ ሰረዘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልል ወሀ ማእድን እና ኢነርጂ ቢሮ በክልሉ በህገ ወጥ መንገድ በማእድን ዘርፍ የተሰማሩ 121 ባለሀብቶች ፍቃድ ሰረዘ።

የቢሮው ሀላፊ አቶ አሰፋ ኩምሳ እንደተናገሩት ፍቃድ ከተሰረዘባቸው በተጨማሪም ለ200 ለሚሆኑት ባለሀብቶች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መሰጠቱን ገልጸዋል።

ቢሮው ይህን እርምጃ የወሰደው በ715 የማእድን የኢንቨስትምንት ፍቃድ በመፈተሽ ህግ፣ አዋጅ እና መመሪያ በሚፈቅደው መሰረት ባለመስራታቸው ነው ሲሉም ተናግረዋል።

አቶ አሰፋ አክለውም፥ወጪ በማይጠይቁ የማእድን ዘርፍም ባለፍት 6 ወራት 52 ሺህ ወጣቶችን በማደራጀት ስራ መፍጠር ተችሏል ብለዋል።

እስካሁንም ወደ ውጭ ኤክስፖርት ከሚደረጉ የማእድን ምርቶች 5 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላይ ገቢ የተገኘ ሲሆን፥ ካለው እምቅ አቅም አንጻር አነስተኛ መሆኑ ነው የተነገረው።

በሰርካለም ጌታቸው