ፕሬዚዳንት ትራምፕ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰንን ከኃላፊነት አነሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰንን ከኃላፊነት አነሱ።

በሬክስ ቲለርሰን ቦታም የሲ አይ ኤ ዳይሬክተር ማይክ ፔምፖንን ተክተዋል ነው የተባለው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰንን በትዊተር ገፃቸው ያመሰገኑት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፔምፖ መልካም ስራዎችን ይሰራሉ ሲሉ ምኞታቸውን ገልፀዋል።

የኤክሶንሞቢል ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩት ሬክስ ቲለርሰን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ከአንድ ዓመት በፊት ነበር።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሆኑት የማይክ ፔምፖ የሲ.አይ.ኤ ዳይሬክተርነት ስፍራ ላይም የመጀመሪያዋ ሴት የሆኑትን ጊና ሀስፔልን በእጩነት አቅርበዋል።

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ