የቱርክ ጦር በኩርድ ታጣቂዎች ቁጥጥር ያለችውን የአፍሪን ግዛት መክበቡ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርክ ጦርና በጥምረት የሚዋጋው የሶሪያ ነፃነት ሀይል የዘመቻቸው ዋና ዓላማ የሆነችውና በሰሜን ሶሪያ የምትገኘውን የአፍሪን ግዛት መክበባቸው ተነገረ።

ጦሩ የአፍሪን ግዛት ከመክበቡ በተጨማሪ በአካባቢው ቁለፍ የሚባል ቦታ መቆጣጠሩም ነው የተነገረው።

 

በጥር ወር በአሜሪካ የሚደገፈውን የኩርዶች ጦር( ዋይ ፒ ጂ)ን ለማጥቃት በአየር እና በምድር ጦሩ ዘመቻ መክፈቱ ተነግሯል።

ቱርክ በአሜረካ የሚደገፈውን ዋይ ፒ ጂ ድጋፍ የሚባለውን የኩርድ ታጣቂ ቡድን በሽብርተኝነት እንደፈረጀች የሚታወቅ ነው።

የኩርድ ታጣቂ ሃይሎች እና ከቱርክ ጦር ጋር ላለፉት 10 አመታት ባካሄዱት ውጊያ ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ ይነገራል።

ተቀማጭነቱን ብሪታንያ ያደረገው የሶሪያ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እንዳስታወቀው ሁኔታው አሳሳቢ በመሆኑ በርካቶች ለስደት መዳረጋቸወን እና በርካቶችም ከተማዋን በመልቀቅ ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል።

አፍሪን ግዛት 350 ሺህ ሰዎች የሚኖሩባት እና ዋይ ፒ ጄ ከተቆጣጠራቸው ከተሞች ትልቋ መሆኗ ተጠቁሟል።

ምንጭ፦ ቢ ቢ ሲ