በኢራን በተመረዘ እንጉዳይ ሳቢያ 11 ሰዎች ሞቱ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢራን የተመረዘ የዱር እንጉዳይ የተመገቡ 11 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ።

በሃገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች እንጉዳዩን ከተመገቡት ውስጥ 11ዱ ለህልፈት ተዳርገዋል ነው የተባለው።

ከዚህ ባለፈም ከ800 በላይ ሰዎች በጽኑ ታመዋል ተብሏል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ሁለት ሰዎች የኩላሊት ንቅለ ተከላ ተደርጎላቸዋል።

በእንጉዳይ ሳቢያ ከሚከሰተው ችግር ጋር ተያይዞ ለሚፈጠር መመረዝ ምንም አይነት ፈዋሽ ህክምና እንደሌለም ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።

በዚህ ሳቢያም የአብዛኛዎቹ ህይዎት አደጋ ላይ መሆኑ እየተነገረ ነው።

በሃገሪቱ በአግባቡ ያልታሸጉና ያልተዘጋጁ እንጉዳዮችን መንገድ ላይ መግዛትና መመገብ የተለመደ ነው።

ዛሬ ከደረሰው የእንጉዳይ መመረዝ ጋር ተያይዞም ሰዎች ያልታሸጉ እንጉዳዮችን እንዳይገዙ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ