የሀገር ውስጥ ዜናዎች (10188)

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የዩኒቨርስቲ መግቢያና የ2ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተናን ለመስጠት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።

ኤጀንሲው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገረው ፥ ዘንድሮ ለፈተና የሚቀመጡት 888 ሺህ የ10ኛ እና 199 ሺህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው።

የዘንድሮው የሁለቱም ደረጃ ብሄራዊ ፈተናም ከግንቦት 19 እስከ 28 ድረስ ባሉት ቀናት ውስጥ ይሰጣል።

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን ዱሬሳ ፥ ለሁለቱም ፈተናዎች  የሚሆን የሰው ሃይል ምልመላ፣  የፈተና ጣቢያ ፣ የፈተና መርሃ ግብርና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል።

ለፈተናው አሰጣጥና ዝግጅትም ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ገልፀዋል።

የፀጥታ አካላትን ጨምሮ ለፈተናው አሰጣጥ ፋይዳ የሚያበረክቱ ከ32 ሺህ በላይ የሰው ሃይል ለፈተናው ዝግጁ መሆኑንም አስረድተዋል።

ኩረጃን ለመከላከል ከትምህርት ቤት ማህበረሰብና ከወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከተማሪዎችና ወላጆች ጋር  በመሆን ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ሲሰራ መቆየቱን  የጠቆሙት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፥ ፈተናውን ለማለፍ መኮረጅን ብቸኛ መፍትሄ አድርጎ በሚያምን ተማሪ ላይ ልዩ አሰራር ተግባራዊ እንደሚያደርግ አንስተዋል።

ቀደም ሲል አንድ ተፈታኝ ለመኮረጅ ወይም ለማስኮረጅ ሲሞክር ሲያዝ ፥ የሚሰረዝበት የተያዘበት የፈተና አይነት ውጤት ብቻ የነበረ ሲሆን፥ በዘንድሮውና በቀጣይ ግን ሙሉ በሙሉ የፈተና ውጤቱ እንዲሰረዝ ይደረጋል ብለዋል።

በተጨማሪም የፈተናውን አላማ ለማሳት የሚሞክሩ ግለሰቦችን ወደ ህግ ለማቅረብ መመሪያ የተዘጋጀ መሆኑንም ተናግረዋል።

አቶ ዘሪሁን አክለውም ፈተናውን በሱዳን ካርቱም እና በሳዑዲ አረቢያ ሪያድና ጅዳ መስጠት እንዲቻል ጣቢያዎች ተዘጋጅተዋል ብለዋል።

ከሶስቱ ሀገራትም 106 የ10ኛ እና 102 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበዋል ነው ያሉት።

በአጠቃላይም የዘንድሮ ተፈታኞች ቁጥርም በ13 እና በ14 በመቶ ብልጫ አለው።

 

በትዕግስት ስለሺ

 

 

 

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ አቅርቦት ተደራሽነቱን  በማሳደግ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት የላቀ ጥረት ማድረግ እንደሚገባው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳሰበ።

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በአዲስ አበባ እየደረሰ ባለው የእሳት አደጋ የቤቶች በዘመናዊ መልኩ አለመገንባትና ህብረተሰቡ ስለ እሳት አደጋ ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆን ለችግሩ አሉታዊ ተጽህኖ እያሳደረ ነው ተባለ ።

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በአሮሚያ ክልል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ጥያቄ ሽፋን በማድረግ በሰው ህይወትና በንብርት ላይ ጉዳት ያደረሱ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራው የቀጠለ መሆኑን ፤ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንና የጋራ የፀረ ሽበር ግብር ሀይል አስታወቀ።

ግብረ ሀይሉ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ለክልሉ ፖሊስ አስፈላጊ የሆነ የክትትልና የምርመራ ድጋፍ እያደረገ ነው።

ሚያዚያ 22 ቀን 2006 ዓ.ም የመማር ማስተማሩን ሂደቱን በማወክ ተማሪዎችን ለሁከትና ለአመጽ ለማነሳሳት ያደረጉት ሙከራ ያልተሳካላቸው ሀይሎች በሃሮማያ ዩኒቨርሰቲ የእግር ኳስ በመከታተል ላይ በነበሩ ሰላማዊ ተማሪዎች ላይ ቦምብ በማፈንዳት አደጋ ያደረሱት ተጠርጣሪዎች ከነግብረአበሮቻቸው በመያዝ ምርመራ እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል።

በተመሳሳይም ከአምቦ እስከ ግምቢ ድረስ ባለት አካባቢዎች ተደራጅተው ወደ ስርቆትና ንብረት ቃጠሎ የገቡ የዘርፊያ ቡድኖችን በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ ቀርበዋል።
 
የቀሩትን አድኖ ለመያዝ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንና ከብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልገሎት እንዲሁም ከፌድራል ፖሊስ ኮሚሽን የጸረሽብር ግብረ ሀይል በመተባበር ክትትል እየተደረገ ነው።

ግብረ ሀይሉ ህብረተሰብ እስካሁን ድረስ ለሰጠው ሁለገብ ድጋፍና እገዛ ያላቸውን ከፍተኛ አድናቆትና ምስጋና የገለጹ ሲሆን ፥  ህብረተሰቡ አሁንም ራሱንና ንብረቱን ከዘራፊዎች ጥቃት እየጠበቀ በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ተጠርጣሪዎቸን ለመያዝ  የሚሰጠውን ጥቆማና መረጃ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ግብረሀይሉ ጠይቋል።