የሀገር ውስጥ ዜናዎች (10419)

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የራያ ቢራ አክሲዮን ማህበር እያስገነባ ያለው የቢራ ፋብሪካ በመስከረም ወር ስራ ይጀምራል ተባለ ።

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ጎንደር እየተከናወነ ያለው የርብ የመስኖ ግድብ ግንባታ በቀጣይ አመት ይጠናቀቃል።

በ2.4 ቢሊዮን ብር በጀት እየተገነባ ያለው ግድቡ ፥ 14 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ የማልማት አቅም አለው።

የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስቴር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገረው ፥ ግድቡ ስራ ሲጀምር 28 ሺህ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

እንዳሉት ለመስኖ ግድቡ ግንባታ የተመደበው በጀት 2.4 ቢልየን ብር ነው ።

በተጨማሪም ከሚሰራበት ቦታ እስከ 50 ኪሎ ሜትር ርቀው ያሉትን የፎገራ አካባቢ አርሶ አደሮች እርሻን ያለማል።

በአማራ ከልል ደቡብ ጎንደር የተጀመረው የርብ የመስኖ ግድብ ግንባታ ፥ አካባቢው የዝናብ አጥረት ያለበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አርሶ አደሩ የሚገጥመውን ችግር እንደሚፈታና ዝናብን በመጠበቅ በአመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚያመርተውን ምርት ከ3 እጥፍ በላይ ከፍ ያደርገዋል ተበሎ ይጠበቃል።

በ2000 ዓ.ም ተጀምሮ በአምስት ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው ይህ ግድብ ፥ በተቋራጮች አቅም ውስነት ፣ በማሽነሪዎች በበቂ ሁኔታ አለመገኘትና የግንባታው ስፍራ አመቺ ባለመሆኑ እስካሁን ሊዘገይ መቻሉን ነው የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ብዙነህ ቶልቻ  የገለፁት።

ይሁንና የተባሉትን ችግሮች ለመቅረፍና ግንባታውን ለማጠናቀቅ ሚንስቴሩ የተለያዩ ድጋፎችንና ክትትሎችን በማድረጉ በአሁኑ ወቅት 64 በመቶ ላይ ደርሷል ነው ያለት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ።

በዚህ አመት መጠናቀቂያ ድረስም አፈጻጸሙን ከ86 በመቶ በላይ የማድረስ አቅድ መያዙንና ይህንንም ለማሳካት የሚያስችል ዋና ዋና ስራዎች መጠናቀቃቸውን  አቶ ብዙነህ ቶልቻ ተናግረዋል።

በቀጣዩ  ዓመትም  የግድቡ ስራ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ብለዋል።

በተያያዘ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስቴር በአሁኑ ወቅት በግንባታ ላይ ያለውና በመስኖ 17 ሺህ ሄክታር መሬት የሚያለማና265 ሺህ ለሚጠጋው የጎንደር ህዝብ የንጹህ ውሃን ማቅረብ የሚችል የመገጭ ገርባ ግድብ ግንባታን በ2.6 ቢልየን ብር ባለፈው አመት ጀምሯል።

በትዕግሰት አብርሃም

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 8 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በአመት 278 ሺህ ቶን ስኳር የማምረት አቅም ያለው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 የስኳር ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቆ በያዝነው አመት ማብቂያ ወደ ምርት ይገባል ተባለ።

የኦሞ ኩራዝ የስኳር ልማት ፕሮጀክት በደቡብ ክልል የኦሞ ወንዝን በሚጋሩት ደቡብ ኦሞ ፣ ቤንች ማጂና ካፋ ዞኖች የሚገኙ ወረዳዎችን ያካልላል።

በፕሮጀክቱ አምስት የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት 250 ሺህ ሄክታር መሬትም ተዘጋጅቷል።

ለስኳር ፋብሪካዎቹ ግንባታ ታስቦ በመከናወን ላይ የሚገኙ የመስኖ ፣ መንገድ እና ሌሎች የመሰረተ ልማትና የማህበራዊ ተቋማት ግንባታም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ከሚገነቡት አምስት ፋብሪካዎች ውስጥ ከሶስቱ ከእያንዳንዳቸው 12 ሺህ ቶን ፣ ከሁለቱ ደግሞ 24 ሺህ ቶን የስኳር ምርት እንደሚገኝም ተጠቁሟል።

ከነዚህም ውስጥ በደቡብ ኦሞ ዞን በግንባታ ላይ ያለው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 የስኳር ፕሮጀክት ከ80 በመቶ በላይ መጠናቀቁ ተገልጿል።

በፕሮጀክቱ ለእርሻ ልማት የሚውል 25 ሺህ ሄክታር መሬትም የተከለለ ሲሆን ግንባታ በያዝነው አመት ማብቂያ ተጠናቆ ወደ ምርት ይገባል ነው የተባለው።

በፕሮጀክቱ ዙሪያ የሚኖሩ 16 አርብቶ አደር ብሄረሰቦች ወደ ከፊል አርሶ አደርነት እየቀየሩ ሲሆን ፥ የማህበረሰቡን ህይወትም ከወዲሁ መለወጥ መጀመሩን በስፍራው ጉብኝት ያደረገችው  ባልደረባችን መሰረት ገዛኸኝ ዘግባለች።

 

 

 


አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 8 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በአዲስ አበባ እየተገነቡ ያሉ የ40 /60 ቁጠባ ቤቶች እስከ ሰኔ 30 ድረስ ይጠናቀቃሉ ተባለ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የቤቶቹ ግንባታ እስከ 58 በመቶ ደርሷል ብሏል።

የኢንተርፕራይዙ ስራ አስኪያጅ አቶ ክንዴ ብዙነህ ፤ በሰንጋ ተራና በክራውን በ2005 ዓ.ም የተጀመሩ የ40 / 60 የቤቶች ግንባታ ከ58 በመቶ በላይ መጠናቀቃቸውን ገልጸው ፥ በ2006 ዓ.ም የተጀመሩ የቤቶች ግንባታም እስከ 20 በመቶ ተጠናቀዋል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ 13 ሺህ 881 ቤቶች በግንባታ ላይ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

በዚህም በሰንጋ ተራ 410 ቤቶች ፣ በክራውን ሳይት 880 ቤቶች በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ ሲሆን ፥ አፈፃፀማቸውም  58 በመቶ እና 46 በመቶ ላይ ይገኛል።

በ2005 ዓ.ም በሰንጋ ተራ ሳይት የተጀመሩ 1292 ቤቶች ፣ በክራውን ደግሞ 5126 ቤቶች ግንባታቸው እየተፋጠነ ይገኛል ተብሏል።
 
ለቤቶቹ ግንባታ 1.5 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን ፥ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ዜጎች የ29.6 ሚሊዮን ብር የገበያ ትስስር መፈጠሩንም ገልፀዋል።

ኢንተርፕራይዙ በ2007 ዓ.ም 15 ሺህ ቤቶችን በመገናኛ ፣ በኢምፔሪያል ፣ሲ ኤም ሲ፣ በቦሌ ቡልቡላና በሌሎችም አካባቢዎች ለመገንባት ዝግጅት እያደረገ መሆኑንም ነው የጠቆሙት።

ስራ አስኪያጁ በመግለጫቸው የመሰረተ ልማት ችግር ፣ የመሬት አቅርቦት እንዲሁም የተቋራጮች የአቅም ውስንነት በክፍተትነት አንስተዋል።

ለ40 /60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች 164 ሺህ 79 ሰዎች ተመዝግበው 2.5 ቢሊዮን ብር ቆጥበዋል።

በትዕግስት ስለሺ